ርእሰ
መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የቱለፋ ሴራሚክ ፋብሪካ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
ፋብሪካው ደረጃውን የጠበቀ ሴራሚክ በማምረት ለኮንስትራክሽን ዘርፉ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።
በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
ሰሜን
ሸዋ ዞን ለኢንዱስትሪ የተመቸ በመኾኑ በርካታ ባለሀብቶች መዋለ ነዋያቸውን ፈሰስ እያደረጉ ይገኛሉ።