Peace & Security

በደ/ብርሃን ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ

ደብረ ብርሃን, ሸዋ
image

ራዕይ

የከተማችንን ፀጥታ አስተማማኝና የተረጋጋ እንዲሆን በማድረግ ለልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ማየት

ተልዕኮ

ወንጀልንና ግጭትን በብቃት መከላከል የሚስችል የፀጥታ መዋቅር በመፍጠር በህ/ሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገስ የፀጥታ አስተባባሪ ሀይል እንዲኖረው በማድረግ በፍትህ አስተዳደር ስርዓት ውስጥ የፀጥታ አካላቱ አስተማማኝ የመፈፀም ብቃት እንዲኖረው ማስቻል ፡፡

በመምሪው የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራቶች

  • • የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ/ማረጋገጥ/
  • • ፖሊስና ሚሊሻን በተገቢው ማስተባበር መምራት
  • • የህዝባችን የሰላም ችግር የሆኑትን ጉዳዮች በመለየት መፍታት
  • • ህዝባችንን የፀጥታው ባለቤት ማድረግ
  • • ጠንካራ የመረጃ ስርኣት በመዘርጋት ወንጀሎች ሳይከሰቱ ማምከን
  • • ግጭትን በማጥናት እርቅ በመፈፀም ወደ ሰላም መቀየር
  • • ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ቅድመ መከላከል ማድረግ
  • • በት/ቤቶች የሰላም ክበባትና ም/ቤቶችን በማዋቀር ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንዲኖር ማድረግ
  • • የሀይማኖት ፎረምና ጉባኤን ወደ ስራ በማስገባት የሀይማኖት መቻቻልና አብሮ መኖርን ማጎልበት/ማዳበር/
  • • የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ በዓላቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በማድረግ የህዝባችንን ሰላም ማረጋገጥ
  • • ሚኒ ካቢኒ ፀጥታ ም/ቤት አማካሪ ም/ቤቶች ወደ ስራ በማስገባት የሰላም ማስለጫ እንዲሆኑ ማድረግ
  • • የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር የህዝብ ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታት
  • • የመከላከያ እና ሌሎች ምልመላዎችን በመመልመል ወደ ማሰልጠና መላክ